Jump to content

ሮማንሽ

ከውክፔዲያ
የሮማንሽ ሥፍራ በደቡብ-ምሥራቅ ስዊዘርላንድ

ሮማንሽ ወይም ሩማንች (Rumantsch) ከስዊስ አገር 4 ብሔራዊ ቋንቋዎች 1ዱ ሆኖ ሌሎቹ 3 ጀርመንኛ ጣልኛፈረንሳይኛ ናቸው። ከሮማይስጥ የታደገ ቋንቋ በመሆኑ የሮማንስ ቋንቋ ቤተሠብ አባል ነውና በተለይ የሚመስለው ፈረንሳይኛ ወይም እጣልኛ ነው። የሚናገረው በግራውብውንደን (ግሪዞን) ካንቶን ስዊስ በሚኖሩ 60,000 ሰዎች ነው። ይህ ከስዊስ አገር ሕዝብ ብዛት 1% ብቻ ሲሆን ከስዊስ አገር ብሔራዊ ቋንቋዎች ሁሉ ትንሹ ነው። እንኳን በስዊስ አገር ከሚኖሩት ስርቦ-ክሮዌሽኛ ተናጋሪዎች ቁጥር ብዛት (111,000) በግማሽ ያንሳል።

በስሜን እጣልያ አገር ዛሬ ለሚናገሩ ቋንቋዎች ለፍሪዩልያንና ለላዲን ቅርብ ዘመድ ነው።

ምሳሌዎች፦

Jau hai num x (ያው አይ ኑም x) - ስሜ x ነው (ስም x አለኝ)።
Jau sun ad uras (ያው ሱን አድ ኡራስ)- በጊዜ ላይ ነኝ።
giuven (ጁቨን) - ወንድ ልጅ፣ giuvens (ጁቨንስ) - ወንድ ልጆች
il giuven (ኢል ጁቨን) - ወንድ ልጁ፣ ils giuvens (ኢልስ ጁቨንስ) - ወንድ ልጆቹ
giuvna (ጁቭና) ሴት ልጅ፣ giuvnas (ጁቭናስ) ሴት ልጆች
la giuvna (ላ ጁቭና) ሴት ልጂቱ፣ las giuvnas (ላስ ጁቭናስ) ሴት ልጆቹ
ያልተለመደ ብዙ ቁጥር፦ um (ኡም) - ሰው፣ umens (ኡመንስ) - ሰዎች

የስዋሰው መረጃ Archived ኦክቶበር 23, 2005 at the Wayback Machine

Wikipedia
Wikipedia