Jump to content

ጉድ ታይምዝ (የቴሌቪዥን ትርዒት)

ከውክፔዲያ
የኤቫንስ ቤትሠብ በ1966 ዓም

ጉድ ታይምዝ (Good Times) ከጥር ወር 1966 ዓም ጀምሮ እስከ 1971 ዓም ድረስ በአሜሪካ የተሰራጨ ቴሌቪዥን ትርዒት ነበር።

በአሜሪካ በጣም ታዋቂና የተወደደ ሲሆን በተለይ በ፪ኛው ምዕራፍ፣ እስከ ፯ኛው ቦታ ደረጃ ድረስ ያዘ። በጠቅላላ እስከ 1971 ዓ.ም. (1979 እ.ኤ.አ.) ድረስ፣ 6 ምዕራፎች ነበሩት።

ጉድ ታይምዝ የሌላው ትርዒት የማውድ ተቀጥያ («ስፒን-ኦፍ») ሲሆን ያውም በፈንታው የለላ ትርዒት የኦል ኢን ዘ ፋሚሊ ተቀጥያ ነበር።

በአስቂኝ ትርኢት ተዋናዮቹ ስለ አንድ ድሃ ጥቁር ቤተሠብ አኗኗር በሺካጎ አሳዩ። እነዚህም ዓመታት ጎፈሬ (ወይም «አፍሮ») የተባለው ጸጉር አሠራር እጅግ ቄንጠኛ ሲሆን ነበርና የዘመኑ ሞድ በትርዒቱ በሙሉ ይንፀባረቃል። ዛሬም በዩቱብ ሊገኙ ይቻላል።