ኢየሱስ
የናዝሬቱ ኢየሱስ ክርስቶስ | |
---|---|
ነዋ በግዑ ለእግዚብሔር ዘይሐትት ወያሰስል ኃጢያተ ዓለም | |
የተወለደው |
በ፩ኛው ዓ.ም. በቤተልሔም ዓመተ ምሕረትም ስለሱ ተቆጠረ |
የእናት ስም |
ማርያም |
የአባት ስም |
እግዚአብሔር አብ (ያሳደገው ቅዱስ ዮሴፍ እንደ አባት) በሰማይ መንፈሳዊ እናት በምድር ሥጋዊ አባት የለውም |
ዓመታዊ ዋና በዐላት |
፱ሲሆኑ ዋና ዋናዎቹ ገና (ልደት) ጥምቀት ስቅለት ትንሳዔ (ፋሲካ) |
ያደገበት ቦታ | ናዝሬት-ገሊላ |
ያረፈው | በ፴፫ኛው ዓ.ም. በእየሩሳሌም |
ከሙታን ተለይቶ የተነሳው | ባረፈ በ፫ኛው ቀን በእየሩሳሌም |
የሚመለከው | በመላው የክርስትና ሃይማኖት እምነት ተከታይ ሕዝብ [1] |
ኢየሱስ (በዕብራይስጥ: ሲጻፍ ישו ፣ ሲነበብ፡ የሹዓ፣ ትርጉሙም፡ የሚያድን ማለት ነው) የክርስትና ሃይማኖት መሰረት ነው። ክርስቶስ ማለት (በግሪክ ቋንቋ ሲጻፍ Χριστός ፤ ይህም መሢሕ ማለት ነው)፤ (በዕብራይስጥ ማሺያሕ ወይም 'የተቀባ' ማለት ሲሆን በተጨማሪም ዐማኑኤል ይባላል ትርጉሙም እግዚአብሔር ከኛ ጋር ሆነ) ማለት ነው ። ከሥላሴ አንዱ አካል ወልድ ኢየሱስ ነው።
ኢየሱሰ በክርስትና ሃይማኖት አንድ አምላክ ከሚሆኑት አብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ ማለትም ከሥላሴ አንዱ ወልድ እሱ ነው ፤ ይህም ወልድ ፣ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ
እንደ ሰው በምድር ተመላልሶ የአባቱን መንግሥት አስተምሮ ለሰው ልጅ መዳን ሲል ራሱን አሳልፎ የሰጠ በመጨረሻም ከሞት ተነስቶ መንፈስ ቅዱስ እንዲተካው አድርጎ ወደ ሰማይ አርጎ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠ ይህን ዓለም ለመፍረድ ዳግም ምፃቱ የሚጠበቅ አምላክ እና ፈጣሪ ነው ። ስለኢየሱስ የበለጠ ለመረዳት አዲስ ኪዳንን በተለይ ወንጌልን በአራቱ ሐዋርያት ፣ በቅዱስ ማርቆስ ፣ቅዱስ ሉቃስ ፣ ቅዱስ ዮሐንስ ፣ ቅዱስ ማቴዎስ የተፃፈውን ያንብቡ ።
ከድረ ገጾቹ አንዱን ለመመልከት እዚህ ላይ ይጫኑ
እንዲሁም አንዳንድ ሃይማኖቶች ደግሞ የእግዚአብሔር መልዕክተኛ ነው ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ ነቢይ ነው ብለው ያምናሉ።
«ኢየሱስ» የሚለው ስም ፦ በግሪክኛ «ኤሱስ» Ἰησοῦ በቀዳማይ እብራይስጥ «ያህሹአ» יְהוֹשֻׁעַ ፣ በደሃራይ እብራይስጥ «ያሱአ» יֵשׁוּעַ ፣ በአረማይክ «ዔሳዩ» ܝܫܘܥ ፤ በቀዳማይ አረብኛ «ዒሳ» عيسى ፤ በደሃራይ አረቢኛ «የሱዐ» يسوع ሲሆን ትርጉሙ ከእብራይስጥ «ያህዌ መድሃኒት ነው» ማለት መድኃኒያለም የሚል ፍቺ አለው፤ በተለይ ኢየሱስ ሰዎች ሲጠሩበት የነበረ የሰው ስም መሆኑን ለማሳየት ለሌሎች ሰዎች አገልግሎት ላይ ውሏል።
የማርያም ልጅ ኢየሱስ ከሌሎች ኢየሱሶች ለመለየት ባደገበት አገር ስም በናዝሬት የናዝሬቱ ኢየሱስ ይባላል፦ ሉቃስ 18፥37።
ከዚህም በቀር «ኢያሱ» (ወይም በግዕዝ «ኢየሱስ»፣ በግሪክ «ኢዬሶውስ»፣ በዕብራይስጥም «ያህሹዓ») የተባሉት ሌሎች ግለሠቦች ከብሉይ ኪዳን እና ከአዲስ ኪዳን ማየት ይቻላል፦
- 1. የነዌ ልጅ ኢየሱስ - በሙሴ ዘመን ይኖር የነበረ ፍጡር ሰው ነው።
- 2. የኢዮሴዴቅ ልጅ ኢየሱስ - በሐጌ ዘመን ይኖር የነበረ ፍጡር ሰው ነው።
- 3. ኢዮስጦስ ኢየሱስ - የጳውሎስ ባልደረባ ነው (ቆላ.4:10-11)።
እንደ ክርስትና እምነትና ወንጌሎች ኢየሱስ ከድንግል ማርያም እና ከመንፈስ ቅዱስ በቤተ ልሔም፣ ይሁዳ ተወለደ። ሳዱላዋ ማርያምና እጮኛዋ ዮሴፍ ለሕዝብ ቁጠራ በይሁዳ ስለ ተገኙ የቤት መጻተኞች ሆነው በጋጣ ተኝተው ነበር፤ ኢየሱስም በግርግም የተኛ እንጂ አልጋ አልነበረም። ገሊላ ግን በስሜን እስራኤል ወይም ሰማርያ ቤተሠቡ የተገኙበት ኢየሱስም የታደገበት ሀገር ነበረ።
ቤተክርስቲያን ቅዱስ ብላ የምትጠቀምባቸው ፬ መጻሕፍት ወንጌሎች በማቴዎስ፣ ማርቆስ፣ ሉቃስና ዮሐንስ እንደተጻፉት የኢየሱስን ትምህርትና ከሞላ ጐደል የሕይወት ታሪኩን ይገልጻሉ።
በነዚህ ወንጌሎች መሠረት ኢየሱስ ሲያስተምር ብዙ ጥቅሶች ይገኛሉ። ለምሳሌ፦
- «የአሕዛብ አለቆች እንዲገዙአቸው፡ ታላላቆቹም በላያቸው እንዲሠለጥኑ ታውቃላችሁ። በእናንተስ እንዲህ አይደለም...» (ማቴ 20፡25)
በዚሁ ጥቅስ ኢየሱስ ዓለሙን እንደ ገለበጠ ተብሏል። በዚያን ጊዜ ይሁዳ በባዕድ አረመኔ ሕዝብ ከባድ ገዥነት ሥር ነበረችና፣ የአይሁዶች ሊቃውንት ከትንቢት የተነሣ ከሮሜ ዕጅ የሚያድናቸውን መሢሕ ይጠብቁ ነበር። ይህ አይነት ትንቢት ቢገኝም ኢየሱስ ያንጊዜ በጦርነት ስላላነሣ የአይሁድ መሪዎች ሊቀበሉት ፈቃደኛ አልነበሩም።
ደግሞ «እግዚአብሔር ምኑን ይፈልጋል?» ለሚለው ለዘመናት ፍልስፍና ጥያቄ በመመልስ ኢየሱስ በብሉይ ኪዳን ትንቢተ ኢሳይያስ ውስጥ ይህን መልስ አገኝቶ ብዙ ጊዜ ያጠቁመው ነበር፦
- «ምሕረት እፈልጋለሁ እንጂ መሥዋዕት አይደለም።»
ለሚሰሙት ተከታዮቹ ግን አዲስ ጥያቄ ጠየቃቸው፣ እንዲህ ሲል፦
- «ሰው ዓለሙን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?» (ማርቆስ 8:36)
በወንጌላት በኩል እጅግ በርካታ ተመሳሳይ ትምህርቶች በቀላሉ ሊነቡ ይቻላል።
ደግሞ ይዩ፦
በተዋሕዶ አብያተ ክርስትያናት እምነት ትምህርት፣ የኢየሱስ ሰብአዊና መለኰታዊ ባሕርይ አንድ (ተዋሕዶ) ነው። ከካልኬዶን ጉባኤ ጀምሮ ግን በሮማ ቤተክርስትያን ትምህርት ዘንድ በሁለት ልዩ ልዩ ሰብአዊና መለኰታዊ ባሕርዮች ተለይቷል። ኢየሱስ ወልድ ሆኖ ከሥላሴ (አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ) አንዱ ክፍል በመሆኑ አምላክ ነው በማለት በንቅያ ጸሎተ ሃይማኖት ይስማማሉ። «ቃሉ ሥጋ ሆነ» ሲባል፣ ፈጣሪው ወደ ፍጥረቱ በሙሉ በመግባት ዓለሙን ለማዳን ኃይልና ፈቃድ እንዳለው ገለጸ ለማለት ነው።
ከዚህ በላይ ስለ ኢየሱስ ማንነት ብዙዎች አብያተ ክርስትያናት ከአዲስ ኪዳን ጠቅሰው እንደሚያስተምሩት የሚከተለውን እንረዳለን
ከሁለት ሺህ ዓመት በፊት በሰው ልጆች ታሪክ ውስጥ አንድ እንግዳ ሰው ብቅ አለ፡፡ ይህ ሰው በአለም ውስጥ የተወለደ ቢሆንም፣ ልክ እንደማንኛውም ሰው ሰብአዊ ማንነት ቢኖረውም ተራ ሰው አልነበረም። ከድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ተፀንሶ ወደ ምድር የመጣው፣ በሰው አምሳል የተገለጠው ራሱ እግዚአብሔር ነው፡፡ ይህ ሰው (የእግዚአብሔር ልጅ) ነው (ሉቃስ 1፡26-35)፣ (ዮሐንስ 1፡1 እና ዮሐንስ 1፡14)።
በብሉይ ኪዳን ስለሚመጣው መሢህ (ክርስቶስ) ሲተነበይ ከመጠሪያዎቹ አንዱ አማኑኤል በዕብራይስጥ «ኢሜኑ» (ከኛ ጋር) «ኤል» (አምላክ) ወይም አምላክ ከኛ ጋራ ማለት ነው። ምድር የእግዚአብሔር መረገጫ እንደ ተባለች (ኢሳይያስ 66:1 እና ማቴ. 5:35) ወደፊት «ከወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ» ለዘላለም የሚነግስ ብለው የተነበዩለት አምላክ የሚሉት እግዚአብሔር ነው።
- የሰው ልጅ ከጠፋበት መንገድ ሊመልስ (ሉቃስ 19፡10)።
- ከጨለማ ስልጣን ሊያድነን (ቆላሲያስ 1፡13)፡፡
- ነፍሱን ለእኛ ቤዛ አድርጎ ሊሰጥ፤ ደሙን ከፍሎ ሊገዛን (ማቴ 20፡28)፡፡
* በሕይወታችን ያለውን የሰይጣንን ሥራ ሊያፈርስ (1ዮሐ 3፡8)፡፡
- የዘላለም ሕይወት ሊሰጠን (1ዮሐ 5፡11፣12)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 3፡16፣17 እና ዮሐንስ 10፡10 ይመልከቱ፡፡
- አዲስ ልደት በመስጠት የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሊያደርገን (ዮሐ 1፡12)፡፡ በተጨማሪ 1ዮሐ 3፡1.2 ይመልከቱ
- ከአብ ጋር የነበረንን ሕብረት ለማደስ (1ዮሐ 1፡3)።
(ዮሐ 14፡7-11)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 1፡18 ይመልከቱ።
- የእግዚአብሔርን ፍቅር አሳየን (1ዮሐ 4፡9፣10)፡፡ በተጨማሪ ሮሜ 5፡8 ይመልከቱ።
- የእግዚአብሔርን ኃይል አሳየን፣ የታመሙትን፣ ሽባዎችን እና አይነስውራንን ፈወሰ (ማቴ 4፡24)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 9፡1-7 ይመልከቱ።
- ርኩሳን መናፍስትን አስወጣ (ማር 1፡34)፡፡ በተጨማሪ ማርቆስ 5፡1-17 ይመልከቱ።
- ተአምራትን አደረገ (ማር 4፡37-41)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 6፡1-21 ይመልከቱ።
- ሙታንን አስነሳ (ዮሐ 11፡43፣44)፡፡
ኢየሱስ በምድር ሕይወቱ እኛ የምንቀበለውን የሕይወት ችግሮች በሞላ አይቷል፤ ስለዚህም ሊራራልን ይችላል። (ዕብ 4፡15)፡፡ በተጨማሪ ማቴዎስ 8፡17 ይመልከቱ።
ኃጢአተኛ ሰዎች በሀሰት ኢየሱስን እንደ ወንጀለኛ ከእንጨት በተሰራ መስቀል ላይ ቸነከሩት፡፡ ራሱን ከዚህ ማዳን ቢችልም፣ አላደረገውም፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር አለሙን የሚያድነው በእርሱ የመስቀል ላይ ሞት ነበርና፡፡ ስዚህ ኢየሱስ ስለ እኛ ሞተ! (ማር 15፡16-39 ያንብቡ) (1ጴጥ 2፡24)፡፡ በተጨማሪ ኢሳያስ 53፡5፣6 ያንብቡ፡፡
ከሦስት ቀን የመቃብር ቆይታ በኋላ እግዚአብሔር ልጁን ከሙታን መካከል አስነሳው! (ማቴዎስ 28 ያንብቡ)፡፡ ትንሳኤውም ጭምር ለእኛ ሲል ነበር፡፡ (ኤፌ 2፡4-6)፡፡ በተጨማሪ ሮሜ 6፡4 ያንብቡ፡፡ አንድእግዚሀቢዬርበሚሄንበአቦበወልድ
በምድር ላይ የነበረውን ሥራ በፈፀመ ጊዜ ኢየሱስ ወደአባቱ ዘንድ ወደሰማይ አረገ፡፡ ይህም ጭምር ለእኛ ነበር፡፡ ምክንያቱም አሁንና ለዘላለሙ ከእርሱ ጋር አብረን ለመኖር ወደ እግዚአብሔር መገኛ የምንሄድበት መንገድ ከፍቶልናል፡፡ (ዕብ 10፡19-22)፡፡ በተጨማሪ ዮሐንስ 14፡1-3 ይመልከቱ። ለተጨማሪ መረጃ የሚከተለውን አድራሻ ይጎብኙ፡ http://bible-question-and-answer.blogspot.com/2012/02/blog-post.html
- ስለ ኢየሱስ የበለጠ ለማወቅ ኢትዮጵያንኦርቶዶክስዶትኮም http://ethiopianorthodox.org/amharic/tiyakenamelse/tiyakenmelse.html የተባለ ድረገጽን ይጎብኙ።
- መጽሓፍ ቅዱስ
- ^ በፕዪው የጥናት መዐከል መሠረት : በ፳፻፲፭ ዓ.ም. በተደረገው ግምት የዓለም ክርስቲያን ሕዝብ በ፳፻፶ ዓ.ም. ወደ ፫ቢሊዮን ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል